2026-09-30
ኦፕንኤአይ “ጂፒቲ-6.1 ሶል” የተባለ አዲስ ሞዴል ይፋ አደረገ
መስከረም /20/2019
ኦፕንኤአይ ጂፒቲ-6 ሶል ከተለቀቀ ከሳምንት በኋላ ከጂፒቲ-6 አስትራ(GPT-6 Astra) ጋር ተቀራራቢ አፈጻጸም ያለው እና ዋጋው ቅናሽ የሆነውን ጂፒቲ-6.1 ሶል የተሰኘውን አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል፡፡
ኩባንያው አዲሱ ሞዴል ለኮዲንግ፣ ለኮምፒዩተር አጠቃቀም እና ለሙያዊ ሥራዎች ከጂፒቲ-6 አስትራ ጋር የሚተካከል ብቃት እንዳለው ገልጾ፤ የግብዓት እና የውጤት (Input/Output) ዋጋውም በአምስት እጥፍ ቅናሽ እንደተደረገለት አስታውቋል፡፡
ጂፒቲ-6.1 ሶል በፕሮግራም አወጣጥ፣ ረጅም ሰነዶችን በመረዳት እና ባለብዙ ደረጃ ሥራዎችን በማከናወን ረገድ ከቀድሞው ጂፒቲ-6 ሶል የተሻለ አቅም አለው።
በተጨማሪም ውስብስብ ጥያቄዎች ሲቀርቡለት ትክክለኛ መልስ የመስጠት መጠኑ ከፍ ያለ ነው፡፡ የተሰጡ ገደቦችን በማክበር እና ያልተፈቀዱ ድርጊቶችን ከመፈጸም በመታቀብ ረገድ የተሻለ አስተማማኝነት አለው።
እንደ ቴክ ክራንች ዘገባ ጂፒቲ-6.1 ሶል ለሁሉም ፕላስ ፣ ፕሮ ፣ ቢዝነስ እና ኢንተርፕራይዝ ተጠቃሚዎች በቻትጂፒቲ ዎርክ እና ኮዴክስ ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።