2026-09-25
ጠንካራ የይለፍ ቃል #password መጠቀም ለምን አስፈለገን?
መስከረም 15/2019
ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም የኢሜይል፣ የባንክ እና የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችን ከሳይበር አጥቂዎች፣ ከማንነት መዘረፍ እንዲሁም ከፋይናንስ አደጋ በመጠበቅ የዲጂታል ህይወትን ደህንነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
ሆኖም በርካታ መለያዎችን በጭንቅላት ማስታወስ ስለሚከብድ፣ ውስብስብ ምልክቶችን በየጊዜው መጻፍ ስለሚያሰለች እና "እኔ ላይ የሳይበር ጥቃት አይደርስም" በሚል የተሳሳተ እምነት ምክንያት፣ ብዙዎች ከጠንካራ የይለፍ ቃል ይልቅ ቀላል እና እንደ ስም፣ የልደት ቀን ወይም «123456» ያሉ ተገማች የይለፍ ቃላትን ለመጠቀም ይገደዳሉ።
ነገር ግን ይህ አካሄድ ለመረጃ መንታፊዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
ስለዚህ ቢያንስ ከ8 እስከ 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ትልልቅና ትናንሽ ፊደላትን፣ ቁጥሮችን እንዲሁም ልዩ ምልክቶችን (@, #, $) ያካተተ ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀምና ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) ማብራት የሳይበር ጥቃት አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
"ስለሆነም ሊደርስብዎ የሚችለውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ዛሬውኑ የይለፍ ቃልዎን ጠንካራ እና በቀላሉ የማይገመት ያድርጉ!"