2026-09-10
የሳይበር ደህንነቷ የተረጋገጠች ዲጂታል ኢትዮጵያን ለትውልድ!
ጷግሜ 5 - "የነገ ቀን"
ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም "የነገ ቀን" በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት ሲከበር፣ ነገን ዛሬ ላይ ሆነን የምንቀርጽበት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግስጋሴያችንን እና በቴክኖሎጂ በራስ አቅም የምትቆም አዲሲቷን ኢትዮጵያን ዕውን የምናደርግበትን ብሩህ ራዕይ የምናስብበት ዕለት ነው።
ይህ ቀን ሀገራችን በዲጂታሉ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ጉልህ ስኬቶች — የዜጎችን ህይወት ያቀለለውን የአንድ ሞሰብ አገልግሎት፣ የነገዋን ሀገር የሚረከቡ አዳዲስ ፈጣሪ ወጣቶችን አቅም የሚገነባውን የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣ እንዲሁም ዘላቂ የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ በኩል የተጓዝንበትን ስኬታማ መንገድ የምናከብርበት ልዩ ቀን ነው።
በተለይም የኢትዮጵያ ልጆች እና ወጣቶች ነገ የሚቀበሏት ሀገር በዲጂታሉ ዓለም ምን እንደምትመስል በስፋት የምንወያይበት ዕለት ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሳይበር ደህንነቷ የተረጋገጠ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ሂደት፤ ሀገራችን በጀመረችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ በመከላከልና በመቀልበስ የሀገሪቱን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ የሳይበር ጋሻ ሆኖ ቆሟል።