2026-09-09
የቡታጅራ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በክረምት የበጎ ፈቃድ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
04/13/2018
ተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎችን በማስተባበር የኢኮኖሚ እጥረት ላላቸው ቤተሰብ ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አበርክቷል።
የኅብር ቀን "ብዝኅነት የኢትዮጲያ ጌጥ" በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 4 በቡታጅራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ውሏል።
ጽ/ቤቱ ወቅቱን ያገናዘበና ለተማራዎች ለወደፊት የዕውቀት ጉዟየው የሚያግዝ በቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሠረታዊ ኮምፒውተር ሳይንስ ፣በኮደርስ እና በስፔስ ሳይንነስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት በማብቃት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፊ ተደርጓል።
የተሰጣቸው ስልጣናም ወቅቱን ያገናዘበና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለወደፋቱ የትምህርትና የስራ እንቅስቃሴያቸው የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል።
የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ አሰፉ ተማሪዎች ከስልጠናቸው ጎን ለጎን ለሌሎች መድረስ አለብን በማለት ያበረከቱት ድጋፍ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
አንድም ተማሪ በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ መነጠል የለበትም በሚል ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በስልጠናው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ማበረታች ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።