2026-08-25
5ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተጀመረ!
ነሀሴ 19 /2018 የ5ተኛው ዙር የኢመደአ የሳይበር ታሐንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም አካል የሆነውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ በይፋ ተጀምሯል።
ፕሮግራሙ ታዳጊዎችን በቴክኖሎጂ እውቀት በማነጽ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት አቅምን ለመገንባት ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየተካሄደ ይገኛል።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ኃላፊ አቶ ሃኒባል ለማ ባደረጉት ንግግር፤ የኢመደአ የሳይበር ታለንት ማዕከል እያፈራ ያለው የሳይበር ታለንት የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ወሳኝ የሰው ሀይል ግብአት መሆኑን አብራርተዋል። በተለይም በቅርቡ የጸደቀውን የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ ተከትሎ፣ ሀገራችን እና የቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ብቁ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን አጥብቀው እንደሚፈልጉ አውስተዋል። በመሆኑም ታዳጊዎች ይህንን ሀገራዊ የደህንነት ኃላፊነት ለመረከብ ራሳቸውን በዕውቀት፣ በስነ-ምግባርና በሀገር ፍቅር ማነጽ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዲን ፕ/ር እንየው ሃድጎ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዘመናችን የዓለም ቁልፍ የመወዳደሪያ አቅም "ልዩ ተሰጥኦ (Talent)" መሆኑን በማስገንዘብ፣ ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮው አኳያ ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኢመደአ ሀገር አቀፍ ታለንትን ለማልማት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው፣ ይህ የዕውቀት ንቅናቄ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽነቱ ሊሰፋ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ ሥልጠናው ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች የሶፍትዌር አቅም እና የሳይበር ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚሠጥ መኾኑን ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው በበኩላቸው፤ ፕሮግራሙ በክልሉ ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዲጂታል ጉዞ እንደሚያፋጥነው ጠቁመው፣ በ2017 ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው ካምፕ በ2018 ዓ.ም ወደ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መስፋቱን አስታውሰዋል። በቀጣይም በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሮግራሙን በማስፋፋት ተደራሽ ለማድረግ ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢመደአ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የሰመር ካምፑ ዓላማ ተማሪዎችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ተግባራዊ የችግር ፈቺነት (Problem-solving) ማሸጋገር ጭምር መሆኑን አብራርተዋል። የካምፑ እውነተኛ ስኬት የሚለካው ተማሪዎቹ ያገኙትን ሁለንተናዊ እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመተርጎም፤ የሕብረተሰቡንም ሆነ የሀገሪቱን ተጨባጭ ችግሮች መፍታት የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አዳዲስ ፈጠራዎችን ማመንጨት ሲችሉ መሆኑን አስምረውበታል።
5ኛው ዙር የኢመደአ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በ6 የተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ይገኛል!
INSA