News details

News Details

Read the full details of the selected news article

2026-08-24

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ መደበኛ ውይይት አደረገ።

(ነሐሴ 18/2018) በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ቴክኒክ ኮማቴ መደበኛ ውይይት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

በውይይት መድረኩ የ2018/19 በክረምት ወራት የተሰሩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን አጠቃላይ ሪፖርት ቀርቦ በጠንካራና መሻሻል ባለባቸው ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የ2018/19 የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ እቅድ አፈፃፀም ለኮሚቴ አባላቱ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ በክረምት ወራት በ16 የስምሪት መስኮች በርካታ የበጎ ፍቃድ ተግባራቶች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በቀጣይም ስራዎች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በተግባር ሂደቱም የባለድርሻ አካላት የቅንጅት ስራዎች መጠናከርና የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተደራሽ መሆን ላለባቸው ወገኖች መድረስ እንደሚገባ ተገልጿል።

በቀጣይ የበጎ ፍቃድ ተግባራቶች ውስንነቶች በመቅረፍ በተሻለ መልኩ መፈፀም እንዳለባቸው በአባላቱ ተመላክቷል።