2026-07-24
የሞባይልዎን እና የኮምፒውተርዎን ሶፍትዌር ማዘመን (Update) ለምን አስፈለገ?
ሀምሌ 17/2018
ብዙዎቻችን በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ "Update Available" የሚል መልዕክት ሲመጣ ጊዜ ስለሚወስድ ወይም ዳታ ስለሚፈጅ ችላ ብለን እናልፈዋለን። ይህ ግን ለሳይበር ጥቃት በቀላሉ ሊያጋልጠን ይችላል!
የቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያዎች አዳዲስ ማዘመኛዎችን (Updates) የሚልኩት አዳዲስ ገፅታዎችን ለመጨመር ብቻ ሳይሆን፣ በስርዓታቸው ላይ የተገኙ የደህንነት ክፍተቶችን (Vulnerabilities) ለመድፈን ጭምር ነው።
የሳይበር ወንጀለኞች እነዚህን ያልተዘመኑ እና ክፍተት ያለባቸውን ሶፍትዌሮች ፈልገው ጥቃት ይሰነዝራሉ። ስለዚህ ስልክዎን፣ ኮምፒውተርዎን እንዲሁም የሚጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች በየጊዜው በማዘመን የሳይበር አጥቂዎችን ቀዳዳ ይዝጉ!