2026-07-23
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ3 ዓመታት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብ ስምምነት እና ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄደ
ወራቤ/ሀምሌ 16/2018 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ያለፉት ሦስት ዓመታት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት መፈራረሚያ እና የአዲሱ በጀት ዓመት ሥራዎችን በይፋ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ።
በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ ክቡር አቶ ሰላሙ አማዶ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የኢኮቴ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ፣ የቢሮ ኃላፊው አማካሪ አቶ ሁሴን ሳኒ እንዲሁም ሙሉ የተቋሙ ሠራተኞች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ያለፉት ሦስት ዓመታት አጠቃላይ አፈጻጸም፣ የተመዘገቡ ድሎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በስፋት ተገምግመው የቀጣይ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን፣ ለ2019 በጀት ዓመት የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል የግብ ስምምነት ከሁለቱም ዘርፎች ጋር ተፈራርመዋል። በዚህም መሠረት ቢሮው የ2019 በጀት ዓመት የሥራ እንቅስቃሴውን በይፋ መጀመሩን አብስሯል።