በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የሣይንስና ሂሳብ የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር እየተካሄደ ነው።

2026-04-08

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የሣይንስና ሂሳብ የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር እየተካሄደ ነው።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የሣይንስና ሂሳብ የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር እየተካሄደ ነው።

(መጋቢት 29/2018)ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ትምሀርት ጽ/ቤቶች በጋራ በመሆን የሳይንስና ሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽንና ውድድር አዘጋጅተዋል።

"ሣይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል" በሚል መሪ ሀሳብ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ባዛር ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰልማን ሳኒ የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ዝግጅቱን ተመልክተዋል።

የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ የተሻለ ጥረት ማድረግና ስራውን ይበልጥ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የበለፀጉ ሀገራት ሚስጥር የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውጤትና ለዘርፉ የሰጡት ልዩ ትኩረት መሆኑን ገልፀው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

የፈጠራ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡ መሆኑንም አቶ አብዶ ገልፀዋል።

የቡታጅራ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሃመድ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ስራ የሚሰራበት ነው ብለዋል።

የፈጠራ ስራዎችን ለውጤት ማብቃት እና የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልል አድርጎ ወደ ውጤት መቀየር ያስፈልጋል ሲሉ አስረድተዋል።

መድረኩ የፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች ልዩ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
Back to News