የቡታጅራ ከተማ የ"ኢትዮ ኮደርስ" ስትሪንግ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

2026-03-04

የቡታጅራ ከተማ የ"ኢትዮ ኮደርስ" ስትሪንግ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

የቡታጅራ ከተማ የ"ኢትዮ ኮደርስ" ስትሪንግ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

የካቲት 13 2018 ​የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ስትሪንግ ኮማቴ የሥልጠና ፕሮግራምን አሁናዊ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ አካሄዷል።

የቡታጅራ ከተማ ምክትል ከንቲባና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ጥላሁን ለሰልጣኞች ምቹ የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት እንዲዘረጋ፣ የኢንተርኔትና የኮምፒውተር ተደራሽነት እንዲሰፋ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው እና እስካሁን ባለው ሂደት የታዩ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል።

ሰልጣኞች የተመቻቸውን የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ስልጠና ዕድል በመሆኑ በአግባቡ ተጠቅመው ራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

የቡታጅራ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለከተማዋ እድገት ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

የኢትዮ ኮደርስ መርሃ-ግብር በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማብቃት ለነገዋ ኢትዮጵያ ዝግጁ ለማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የኢትዮ ኮደርስ መርሃ-ግብር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን የኮዲንግና የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ ዕድል የፈጠረ ነው"።

የኮሚቴው አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ የቀሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የክትትል ስራው በተገቢው በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
Back to News