2026-02-12
የቡታጅራ ከተማ ገጽታ በወንዝ ዳርቻ ልማት ደምቃለች
በከተማው ከሚገኙ ትላልቅ ወንዞች መካከል የእሪንዛፍ ወንዝን ተከትሎ 42 ሄክታር የወንዝ ዳርቻ ልማት ለማልማት " HH" በተባለ አማካሪ ድርጅት ዲዛይን በማሰራት በተለያዩ ምዕራፎች ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል ያሉት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ፣በመጀመሪያው ምዕራፍ ከ4 ሄክታር በላይ የወንዝ ዳር ልማት መሰራቱን ገልጸዋል ።
ከእሪንዛፍ ድልድይ እስከ ፀበል ወይም ቡታጅራ ካምፓስ ድረስ የሚሸፍነው የወንዝ ዳርቻ ልማት ትልቅ ተፈጥሮ የቸረው አካባቢ ሲሆን እሴት በመጨመር ለከተማው ብሎም ለክልሉ ትልቅ አቅም የሚሆን ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል ።